ቀን ሐምሌ 28/2017 ዓ/ም
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በኢ-ስኩል ምንነት፣አስፈላጊነት እና አጠቃቀም ዙሪያ ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የኮሌጁ የሰው ሀብት ልማት ስራ አመልራር ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ናሁሠናይ በርጋ ሲሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል በስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግኝትና በቀጣይ ለሚኖር ስራዎች ውጤታማ መሆን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፍዋል።
የኮሌጁ የኢ-ስኩል ፎካል የሆኑት አቶ ዳዊት ሙሉጌታ የስልጠናው ዋና አላማ ቢሮው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሰራተኞችን አቅም በመገንባት ከወረቀት ነፃ የሆነ አገልግሎት ለመስጠትና ዲጅታላይዜሽን ለማስፋት ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።
ስልጠናውን ከተጋባዥ አሰልጣኝና የኮሌጁ የኢ-ስኩል አሰልጣኞች በጋራ የሰጡ ሲሆን ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሲሆን በዛሬው ዕለት የተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይ በሌላ ዙሮች የሚቀጥሉ መሆኑ ተገልፆል።
"የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን"