Call us:
+913038373
|
Mail us for help:
bolemanufacturing@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Lemi Kura Manufacturing College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Status
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Login
Online Admission
ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና እና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና እና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
31st December, 2025
ቀን ታህሳስ 22/2018 ዓ/ም
ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና እና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም እና በ2018 ዓ/ም ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና እና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሀ-ግብር አካሄዷል፡፡
በመርሀ-ግብሩ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው የእንኳን ደህና መጣጩህ መልክታቸውን በማስተላለፍ ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓት ከ130 በላይ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ በትብብር እንደሚሰራ በመግለፅ የመርሀ-ግብሩ ዋና ዓላማ ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና የስራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎችን ለማመስገንና እውቅና ለመስጠት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታደለ ሀይሉ እና ጥሪ የተደረገላቸው የካምፓኒ እና የኢንዱስትሪ ተወካዩዎች እንዲሁም የኮሌጁ አካዳሚክና ማናጅመንት አባላት ተገኝተውበታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታደለ ሀይሉ እንደገለጹት ኮሌጁ ጥራት ያለው ስልጠና ለማሰልጠንና ራዕይና ተልእኮ ለማሳካት የካምፓኒዎችና የኢንዱስትሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው በጋራና በትብብር መስራቱን በማስቀጠል በቀጣይም ከዚህ በላይ በትብብር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ ኮሌጁ የ10 አመት ታሪካዊ ዳራውን የሚያሳይና እና የዕለቱን መርሃ-ግብር አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ በኮሌጁ ዋና ዲን በሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ ተሳታፊ የካምፓኒ እና የኢንዱስትሪ ተወካዩዎች ሀሳብና አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን በተነሱ ሃሳቦች ላይም በአመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(ዶ/ር) ኮሌጁ በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች መሰረት አድርጎ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በማድረግ የኢንዱስትሪዎችን ምርትናምርታማነታቸውን በማሳደግ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ኮሌጅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ኮሌጁ ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና በመስጠትና የስራ እድል በመፍጠ ረገድ ከ1-3 ለወጡ ካምፓኒዎችና ኢንዱስትሪዎች የዋንጫና እና የሰርተፍኬት ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››
.