ቀን ሰኔ
25/2017 ዓ/ም
ለመደበኛ ሰልጣኞች በE-SCHOOL ዙሪያ ማስጨበጫ ስልጠና መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ለመደበኛ ሰልጣኞች በE-SCHOOL ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መርሀ-ግብር አካሂዷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የኮለጁ E-SCHOOL Focal Person የሆኑት አቶ ዳዊት ሙሉጌታ ሲሆኑ ስለ E-SCHOOL ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሰልጣኞች ወደፊት ማንኛውንም አገልግሎት ማግነት የሚችሉት በዚሁ ሲስተም ላይ የተመዘገበ ሰልጣኝ መሆኑን አውቆ ሁሉም የኮሌጁ ሰልጣኞች በሲስተሙ መመዝገብ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በተደረገው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ- ግብር ወ 59 ሴ97 አጠቃላይ 156 መደበኛ ሰልጣኞች ተገኝተዋል።
የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን (ዶ/ር) ዘመኑ የዲጂታላዜሽን እንደመሆኑ መጠን ሰልጣኞች በኮሌጁ የሚተላለፉ ምንኛውም መረጃዎችን ለማግኘት በሲስተሙ መመዝገብ እንዳለባቸው ገልፀዋል።
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››