Call us:
+913038373
|
Mail us for help:
bolemanufacturing@aatvetb.edu.et
|
Help center
360° Support - We are here to assist you.
Lemi Kura Manufacturing College
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
Online Admission
Back
Online Admission
Application Form
Registration Form
Status
Announcement
Back
Announcement
News
Notice
Event
Resource
Back
Resource
Publication
Policy&Strategy
Educational Statics
Legal Document
Gallery
Support
Back
Support
Submit Ticket
My Tickets
More
Service
About
Contact Us
Login
Online Admission
‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››
‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››
09th February, 2026
ቀን የካቲት 02/2018 ዓ/ም
‹‹በአዲሱ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ለሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ››
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም ትምህርታቸውን ላጠናቀቁና በ2018 ዓ.ም ለሚያጠናቅቁ ሰልጣኞች በአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አተገባበር ዙሪያ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ይህ ስልጠና የተዘጋጀው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እየተተገበረ ባለው አዲስ ፖሊሲ መሠረት ሰልጣኞች ስለ አዲሱ የምዘና ሥርዓት፣ ስለ ዝግጅት ሂደቶች እና ስለ ምዘናው አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ከወዲሁ እራሳቸውን እንዲያዘጋጁና በምዘናው ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አይናለም አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ የሰልጣኞችን ተግባራዊ ክህሎት እና በገበያ ላይ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በመግለፅ የሙያ ብቃት ምዘናው (COC) ሰልጣኞች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ወሳኝ መሳርያ መሆን ገልፀዋል፡፡
በስልጠናው በ2017 ዓ.ም ት
ምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ወደ ሥራው ዓለም ከመሰማራታቸው በፊት ይህንን ምዘና ማለፍ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም ለሚያጠናቅቁት ደግሞ ቅድመ-ዝግጅት እንዲያደርና ኮሌጁም ለሰልጣኞቹ አስፈላጊውን ግብዓትና ድጋፍ በማሟላት ለምዘናው ዝግጁ እንዲሆኑና በምዘናው ብቁ እንዲሆኑ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››
.