ሰኔ 30/2017 ዓ.ም
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከየስልጠና ዘርፉ እና ከየስራ ክፍሉ የተወጣጡ ከ24 በላይ ለሚሆኑ የኮሌጁ ሰራተኞች የISO 21001፡2018 ትግበራን ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቱዩት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
ስልጠናውን ያስጀመሩት የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(ዶ/ር) ሲሆኑ የስልጠናው ዋና አላማ የISO ትግበራን በተቋማችን ዕውን ለማድረግ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ለማግኘት ያለመ ስልጠና መሆኑን ጠቅሰው ይህን ተግባር እውን ለማድረግ ሁሉም የስልጠና ተሳታፊ የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ መከታተልና ወደ ተግባር መቀየር እንዳለበት በማሳሰብ መልካም የስልጠና ጊዜ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፅዋል።
ስልጠናወን የሰጡት "የISO 21001:2018 ትግበራን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የቴክኒካል ድጋፍ የሚያደርጉ ከኢኒስቲትዩቱ በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሲሆን ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ተገልፃል።
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››