Announcement የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ

የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ

04th July, 2025

ቀን  ሰኔ 27/2017 ዓ/ም


የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ፡፡


የለሚ ኩራ የማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ  አጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር በመሆን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  ውይይት አካሂዷል፡፡


ኮሌጁ  በበጀት አመቱ  በእቅዱ  መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን፣ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን  እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያካተተ ሪፖርት በኮሌጁ ዋና ዲን በሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር)   አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

      

የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ተሳታፊ የኮሌጁ ማህበረሰብ በቀጣይ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችና መተግበር የሚኖርባቸው አሰራሮች ላይ  ጥያቄዎችና አስተያየቶች አቅርበው በአመራሮች  ምላሽ  እና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


""የለሚ ኩራ የማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን""



.

Copyright © All rights reserved.

Created with