የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የማናጅመንትና ፕሮሰስ ካውንስል አባላት በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ያጠናውን የግብ ስኬት የዳሰሳ ጥናት ዉጤት አቀረበ፡፡
ኮሌጁ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በ2017 በጀት ዓመት እራሱን የቻለ ኮሚቴ በማዋቀር ያጠናውን የግብ ስኬት የዳሰሳ ጥናት ውጤት በዛሬው ዕለት አቅርቧ፡፡
የ2017 ዓ/ም የግብ ስኬት የዳሰሳ ጥናት የጥናቱ ዋና አላማ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት የግብ ስኬት የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ አፈፃፀምን ለመለካት እና ለቀጣይ የ2018 ዓ/ም የመነሻ እንዲሆን ያለመ የጥናት ውጤት መሆኑን የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
የግብ ስኬት ጥናቱ የተለያዩ አላማዎች የሰነቀ ሲሆን የግቦችን አፈፃፀም ያለበተን ሁኔታ መዳሰስ፣የግብ ስኬት ተግዳሮቶችን መለየት እና የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ የሚሉ ዓላማዎችን የያዘ ጥናት መሆኑ በጥናቱ ተገልፃል፡፡
የተጠናው የግብ ስኬት የዳሰሳ ጥናት ለወደፊት ለሚጠኑ ጥናቶች እንደግብአት የሚረዳ መሆኑን ጠቅሰው ያለንን ጥንካሬ እና ድክመት በመለየት እና በማስተካከል የተጠያቂነ ስሜት ለመመስረት የሚያስችል የጥናት ውጤት መሆኑን የኮሌጁ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››