Announcement የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ፡፡

23rd July, 2025

የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ተካሄደ፡፡

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  ውይይት አካሂዷል፡፡

ኮሌጁ  በበጀት አመቱ  በእቅዱ  መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን፣ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተወሰዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን  እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያካተተ ሪፖርት በኮሌጁ ዋና ዲን በሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ውይይቱን የመሩት የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ  እና የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን (ዶ/) ሲሆኑ የውይይቱ ዋና ዓላማ ኮሌጁ በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠልና በድክመት የታዩትን ለማረም ያለመ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልፃል፡፡

      

በቀረበው ሪፖርት መነሻነት ተሳታፊ ባለ ድርሻ አካላት ሐሳብና አስተያየቶችን  ያነሱ ሲሆን በተነሱ ሀሳቦች ላይ የኮሌጁ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራትና ያለውን አጠናክሮ ለማስቀጠል  የሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረትና ትብብር ሊኖር እንደሚገባ  ተጠቁሟል።  

‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with