Announcement በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር ተካሄደ፡፡

በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር ተካሄደ፡፡

08th July, 2025

ቀን  ሰኔ24/2017 /

 

በለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 2017 / አጠናቃቂ ሰልጣኞች  የስራ ፈጠራ  ሀሳብ ውድድር ተካሄደ፡፡

 

የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ  ከአስካማር ኮንሰልቲንግ /የተ/የግል ድርጅት ጋር በመተባበር 2017 አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን ለውድድር  አቅርበዋል፡፡

 

በውድድሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የኢ/////ዲን የሆኑት ሙሉጌታ አለሙ(/) ሲሆኑ ሰልጣኞች በዚህ ልክ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ይዘው መቅረባቸው የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው  ሰልጣኞች በዚህ ልክ  የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን ካሳዩ ኮሌጁ የሚጠበቅበትን የቦታና መሰል ግብዓቶችን የማሟላት  ኃላፊነቱን የሚወጣ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

 

በውድድሩ 5 የስራ ፈጠራ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል በጋርመንት ዘርፍ  የተማሪ ዩኒፎርም እና ቲሸርቶችን መስራፍ ፣በሆቴል ዘርፍ  የካፌ አገልግሎት፣ በአይሲቲ የሶሻል  ሚዲያ  የግራፊክስ ዲዛይን የሀበሻ ዳቦ  እንዲሁም ፊስታልን ሙሉ ለሙሉ የሚተካ የሳክ ኮሮጆ ማምረት የሚሉ  የስራ ፈጠራ ሀሳቦች ለውድድር ቀርበዋል፡፡

 

በውድድሩ  ማጠቃለያ  የሰልጠናና አካዳሚክ ጉዳዩች /ዲን የሆኑት / ትዕግስት አይናለም  የቀረቡት የስራ ፈጠራ ሀሳቦች  ኮሌጁ ካለው  አቅም አንፃር እንጅ ሁሉም የስራ ፈጠራ ሀሳቦች ገዥ እና ጥሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

 

‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

 

.

Copyright © All rights reserved.

Created with