Online Admission 16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ለስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች፣ ለዳኞች እና ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ (ኦረንቴሽን) ሰጠ።

16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ለስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች፣ ለዳኞች እና ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ (ኦረንቴሽን) ሰጠ።

10th February, 2026

ቀን የካቲት 03/2018 ዓ/ም


የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ የስራ ሂደት  16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክንያት በማድረግ ለሚካሄደው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር ስኬታማ እንዲሆን ለስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች፣ ለዳኞች እና ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ (ኦረንቴሽን) ሰጠ።


የመድረኩ ዓላማ በውድድሩ ወቅት ሊከተሏቸው ስለሚገቡ የዳኝነት መመሪያዎች፣ ስለ ውጤት አሰጣጥ ግልጽነት እና ተያያዥ ቅሬታዎች ቢነሱ ሊፈቱ የሚችሉበትን ስርአት ለመዘርጋት እና ውድድሩ ፍጹም ፍትሃዊ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ  ኦረንቴሽን ነው፡፡


 የኢ/ኤ/ቴ/ሽ/ም/ዲን የሆኑት  ሙሉጌታ አለሙ (ዶ/ር)  የክህሎት ውድድሩ ውጤታማ የሚሆነው ዳኞችና አስፈጻሚ አካላት በታማኝነትና በሙያዊ ስነ-ምግባር ስራቸውን ሲወጡ በመሆኑ ለተወዳዳሪ ሰልጣኞች ተገቢውን ምዘና በመስጠት በኩል የዳኞች ሚና ወሳኝ በመሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊከናወን ይገባል በማለት  ለተሳታፊዎቹ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።


https://bmc.sims.aatvetb.edu.et/frontend/post/-16-


‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››

.

Copyright © All rights reserved.

Created with