ቀን ሐምሌ 21/2017 ዓ/ም
የእውቅናና የምስጋና መርሀ-ግብር ተካሄደ!
የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በ2017 በጀት አመት በቴክኖሎጅ፣በአይሲቲ፣በክህሎት ውድድር፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አሰልጣኞች፣ዳይሬክቶሬቶች፣ቡድን መሪዎች፣አስተባባሪዎች፣እንዲሁም ባለሙያዎች የእውቅናና የምስጋና መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡
በመርሀ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት ታደሰ መኮንን(ዶ/ር) ሲሆኑ በመክፈቻ ንግግራቸው የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ኮሌጁ የዛሬ አስር አመት መመስረቱን በመጥቀስ በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ብዛት ያላቸው ሰልጣኖችን ተቀብሎ በተለያየ መርሀ ግብር በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋም ልማት ዘርፍ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ ፣ የክላስተር ኮሌጆች ዋና ዲኖች ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተውበታል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋም ልማት ዘርፍ የሆኑት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በርካታ ተልዕኮችን በማሳካት ለከተማ አስተዳደሩ የጀርባ አጥንት በመሆን ወጣቱን ስራ ፈጣሪ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው ከጣይ በ2018 ዓ/ም ከዚህ የበለጠ ትጋት እና ውጤታማነት መሆን ያስፈልጋል በማለት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፅዋል።
በመርሀ-ግብሩ በበጀት ዓመቱ ፣በቴክኖሎጅ፣በአይሲቲ፣በክህሎት ውድድር፣በጥናትና ምርምር እንዲሁም ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አሰልጣኞች፣ዳይሬክቶሬቶች፣ቡድንመሪዎች፣አስተባባሪዎች፣ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዚህ በፊት በአመራርነት ሲያገለግሉ ለቆዩ አመራሮች የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት፣የዋንጫ ሽልማቶችን በማበርከት የእለቱ መርሀ-ግብር ተጠናቋል፡፡
‹‹የለሚ ኩራ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ኮሙኒኬሽን››